- Post:ICT Admin
- Tuesday, November 11, 2025
- Read 289
- 289
- 265
ዜና ሻሎም
ሻሎም ኮሌጅ፣ መምህራን ፣ ሠራተኞች፣ የኮሌጅ ማናጅመንት አባላት አና የኮሌጅ ቦርድ አባላት በተገኙበት፥ አስደናቂ የህዝብ ንግግር ተካሄደ። የሕዝብ ንግግሩን ያካሄድት ሳይንቲስት ዶ/ር ጥላዬ ታደሰ ንግግራቸውን ያቀረቡት "Exploring The Cosmos: Why AStrophysics Matters For Our Future" በሚል ርእስ ሲሆን፥ ለሀገር እና ለማሕበረሰብ የሚጠቅምና ችግር ፈቺ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዳሰሳ አድርገው ንግግራቸውን አቅርበዋል። ሳይንተኢስቱ ባደረጉትም ንግግር፥ ኢትዮጲያ ብዙ ተስፍ እንዳላት ለማመልከት ችለዋል። ሳይንቲስቱ ዶ/ር ጥላዬ ታደሰ በ አሜሪካን ሀገር ናሳ የምርምር ጣቢያ በጆንሰን እስፔስ ሴንተር (NASA'S Johnson Space Center) ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ለኮሌጁ ማሕበረሰብ ካካፈሉት ጉዳዮች መካከል፥ ለሀገር የምርምር ሥራ ተቀዳሚ ስፍራ ሊሰጠውና የዘርፉ ዝንባሌ ላላቸው: የሕዋ ሳይንስ ተመራጭ የትምህርት መስክ እንደሆነ አሰረድተዋል። የመሬት ከሌሎች ፕላኔቶች ትንሽነቷ፥ የከዋክብት ብዛት፣ የጨረቃ እና የፀሀይ ሀይል አጠቃቀም አና ብርሀን እንዲሁም የእያንዳንደኡ ፕላኔት ርዝመትና ለሰው ልጆች ያላቸው ጠቀሜታ እና የሰው ልጆች በምርምር ብዛት በቀጣይ ጠፈር እንዴት የሰው ልጅ መቆያ መሆን እንደሚትችል በንግግራቸው በስፋት ተብራርቷል። በንግግር ጉባኤው ተማሪዎች መምህራን ሰራተኞች፣ እና የቦርድ አባላት ከነልጆቻቸው ጋር ተገኝተው በዶ/ር ጥላዬ የህዋ ሳይንስ የህዝብ ንግግር ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎችም ለዶ/ር ጥላዬ ያላቸውን አድናቆትና አክብሮት እንዲሁም እቲዮጲያ የእውነት እንደጥላዬ ያሉ ብዙ ተስፋዎች እንዳሉ መስክረው የእለቱ ጉባኤ ተጠናቋል።