• Post:ICT
  • Tuesday, November 11, 2025
  • Read 289
  • 289
  • 265

ዜና ሻሎም

ሻሎም ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በማስተርስ፣ በመጀመሪያ ድግሪ እና በዲፕሎማ መርሀ ግብር ሲያስተምራቸው የነበረውን በርካታ ተማሪዎቹን በዛሬው ቀን ነሀሴ 17/2017 ዓ.ም በሴንትራል ሆቴል ሀዋሳ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ለአምስተኛ ጊዜ አስመርቋል። በዕለቱ የሻሎም ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፀጋዬ ማቴዎስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው በንግራቸውም ተመራቂ ተማሪዎች በቀጣይ ምዕራፋቸው በተመረቁበት የትምህርት መስክ ሀገራቸውን በታማኝነት በትጋት እንዲያገለግሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። እንዲሁም የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ብቃት ምዘና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። አቶ ቴዎድሮስ በምረቃው ተገኝተው ተመራቂ ተማሪዎች ት/ት በዚህ የማያበቃ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ ፣ ተመራቂ ተማሪዎች ማንኛውንም ስራ ተግተው እንዲሰሩና ቤተሰብን እና ሀገርን እንዲወዱ ምክር አዘል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በተጨማሪም የክብር እንግዳው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሜዳሊያ እና የዋንጫ ሽልማት አበርክተዋል። ሀዋሳ፣ ሲዳማ፣ ኢትዪዺያ።

Recommended

  • Tuesday, November 11, 2025
  • By ICT

ዜና ሻሎም

ሻሎም ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ5ኛ ዙር ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

Read More
  • Tuesday, November 11, 2025
  • By ICT Admin

ዜና ሻሎም

በሻሎም ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፤ ለኮሌጁ ማሕበረሰብ የሕዝብ ንግግር (Public Speech) በእውቁ ሳይንቲስት ዶ/ር ጥላዬ ታደሰ ተካሄደ።

Read More
  • Tuesday, November 11, 2025
  • By ICT

ዜና ሻሎም

በሻሎም ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ሥልጠና ተሰጠ።

Read More